Our Main Goal የ እኛ ዋና አላማችን
We all ye kebena sefer lijoch living abrod planning once a year reunion and creating unforgettable memories for everyone involved.
Our Events የእኛ ድርጊቶች
All ye kebena sefer lijoch reunion will be 13500 Stargazer Ln in Silver Spring MD
Contact Us አድራሻችን
Contact us for our upcoming reunion, with our E-mail myrootkebena@gmail.com call us we are available
ዜና ዕረፍት ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን አጣች። ውዷ እህታችን የማርያምወርቅ አክሊሉ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ትናንትና፣ ሰኞ፣ ጥቅምት 4 ቀን፣ 2017 ዓ/ም (October 14/2024) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታናለች ። የቀብሯ ስነስርዓትም ዛሬ፣ ማክሰኞ ጥቅምት 5 ቀን ተፈጽሟል። የማርያምወርቅ በጣም ትሁት፣ ትልቅ ትንሹን አክባሪ፣ ከሁሉም ተግባቢ፤ የሰው ፍቅር ያላትና በጣም ቅን የቀበና ምርጥ ልጅ ነበረች። ቸሩ ፈጣሪ የእህታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቧና ወዳጅ ዘመዶቿ ሁሉ መፅናናትን ያድልልን።
የ መላው የቀበና አብሮ አደጎች የ፩፩ኛ ዓመት በዓላችንን እንድናከብር ከ መላው ቤተሰብዎ ጋር ጋብዘነዎታል።
የቀበና ኮሪያ ሰፈር አብሮ አደጎች ማህበር በ2.8 ሚሊዮን ብር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር የለይቶ ማቆያ ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ሲያስቀመጡ የሚያሳይ ፡፡
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ውድ ልጇን አጣች
ቀበና ካፈራቻቸውና ካሳደገቻቸው የፍቅር ሰዎች መካከል አንዱ የነበረውና በትንሽ ትልቁ ተወዳጅ የነበረው ወንድማችን ሥዩም አጎናፍር ባደረበት ህመም ምክንያት በአሜሪካ ሃገር ለረዥም ጊዜ
በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ሰኞ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል።ሥዩም አጎናፍር በቀድሞው የመንገድና ትራንስፖርት ሚኒስቴር መ/ቤት ውስጥ በአዎሽ አርባና በተለያዩ
ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ለረጅም ዓመታት በኃላፊነት ቦታ በቅንነትና በታማኝነት ሃገሩንና ወገኑን ካገለገለ በኋላ ቀሪ ዘመኑን በግል የሥራ ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ ነበር። በነዚህ ሁሉ የአገልግሎት
ዘመናት ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ተግባቢ፣ ቁምነገረኛ፣ ቀልድ አዋቂና ተጨዋች ሰው ነበረ። በኖረባቸው፣ በሠራባቸውና በደረሰበት ቦታ ሁሉ ከሰው ጋር በቀላሉ ተግባቢ ትንሽ ትልቁን ከራሱ አስበልጦ
የሚያይ እጅግ በጣም ሰው ወዳድና አክባሪ ነበር። ሥዩም በተለያዩ የግል የትራንስፖርት ንግድ ሥራዎች ላይ በተሰማራባቸው ዓመታት ሁሉ ለበርካታ ወገኖቹ የሥራ ዕድል ከፍቶላቸዋል።
የተቸገሩ ወገኖቹንም በመርዳት የሚታወቅ ቸርና ርህሩህ ሰው ነበር። ለወላጅ እናቱ ለወይዘሮ ማሚቴ ዳኜ፣ ለባለቤቱ ለወ/ሮ ክብሯ መኰንንና ለልጆቹ፣ ለመላ ቤተሰቡ፣ እህትና ወንድሞቹ
እንዲሁም ለጓደኞቹና ወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሄር መፅናናትን እንዲሰጣቸው ከልብ እንመኛለን። በቨርጂኒያ፣ ዲሲና ሜሪላንድ አከባቢ የምትኖሩና የሀዘኑ ተካፋይ ለመሆን የምትችሉ
ዕሮብና ሐሙስ (07/05 & 07:06) በደብረ መድኅኒተ እየሱስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
13450 Minnieville Rd, Woodbridge, VA 22192
ለቅሶ መድረስ ትችላላችሁ። የሥዩም ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቹ በዚህ ቤተክርስቲያን ከላይ በተጠቀሱት ቀናት (ዕሮብና ሐሙስ፣ 07/05 & 07/06) ከ11:30 AM እስከ 7:30 PM ድረስ እንግዶችን ይቀበላሉ።
ዜና ዕረፍት ቀበና ሌላ ልጇን አጣች በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለረጅም አመት በሂሳብ ክፍል ያገለገለች ውድ እህታችን ሙላቷ ውብሸት በህክምና ስትረዳ ቆየታ ሰኔ 13 ቀን 2014 አርፋለች። ሙሏቶ ውብሸት በቀበና ከናቷ ። ወ/ሮ ማሚቴ ደሚሴ ከአባቶ ከሻንበል ውብሸት አየለ በቀበና የተወለደች ትንሸ ትልቁን አክባሪ፣ ትሁትና ከሁሉም ጋር ተግባቢ ቁምነገረኛ በሙያዋ የተቸገሩትን ትረዳ የነበረ እህት ነበረች ። ፈጠሪ እግዚአብሄር የእህታችንን ነፍስ ይማርልን፣ በአጸደ ገነትም ያኑርልን። እንዲሁም ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን። አሜን
ዜና ዕረፍት ቀበና ሌላ ልጇን አጣች ቀበና ካሳደገቻቸው የፍቅር ሰው ከሆነት ውጥ አንዶ የሆነችው እህታችን በዛወርቅ ወልደ ጎርጊስ እረቡ ግንቦት 16 2015 ዓ ምህረት በደረሰባት ድንገተኛ ህመም አርፋለች። ውድ እህታችን በዛወርቅ ወ/ጊዮርጊስ ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ አሣ ሀብት ለማት ኮርፕሬሽን ዉሰጥ በተለያየ ሀላፊነት የሰራች ፣ ከስራ ባልደረቦች ጋር ተግባቢ ፣ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፣ ትሁትና ከሁሉም ጋር ተግባቢ ቁምነገረኛ ቀልደኛና ተጨዋች እህት ነበረች ። ፈጠሪ እግዚአብሄር የእህታችንን ነፍስ ይማርልን፣ በአጸደ ገነትም ያኑርልን። እንዲሁም ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን። አሜን
ዜና ዕረፍት ቀበና ሌላ ውድ ልጇን አጣች። አብሮ አደግ ወንድማችን አለምዘውድ ያለው ባደረበት ህመም ለረዥም ጊዜ በወንድሞቹ እና እህቶቹ ድጋፍ ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ዛሬ ማረፉን ሰምተናል። ኣለምዘውድ ትንሽ ትልቁን ኣክባሪ ትሁት ከሁሉ ጋር ተግባቢ ተጨዋሽ ነበር ቸሩ እግዛብሄር ነብሱን ከደጋጎቹ ጎን ያስቀምጥልን ቀብሩም ነገ የካቲት 10 2015ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ስዓት መገናኛ (ሾላ) በሚገኘው የካ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን መሆኑ ተገልጿል። ኣለምዬ እግዚአብሔር ነብስህን ይማር ለቤተሰቦቹም መፅናናትን ይስጥል ኣሜን!
ቀበና ሌላ ልጇን አጣች ውድ ዲዲ በሪሁን ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ አርብ እለት መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ/ም Friday 24/ 2023 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታናለች። ዲዲ በሪሁን አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቶን አጠናቃ ትዳር ይዛ በፊላንድ ለረጅም አመት ከውድ ባለቤቶና ከልጆቾ ጋር ትኖር ነበር። ዲዲ በሪሁን ትንሽ ትልቁን አክባሪ፣ ትሁትና ከሁሉም ጋር ተግባቢ ቁምነገረኛ የተቸገሩትን ትረዳ የነበረች ቀልደኛና ተጨዋች ውድ እህታችን ነበረች ። የቀብር ስርአቱ አርብ March 3/ 2023 ቀን በስዊድን ይደረጋል እንዲሁም የፀሎት ስርአት በቀበና አብሮአደግ ጓደኞቾ በቦሌ አዲሱ ሚካኤል ይደረጋል። ፈጠሪ እግዚአብሔር የእህታችንን ነፍስ ይማርልን። በአጸደ ገነትም ያኑርልን። እንዲሁም ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቿ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን። አሜን
ዜና እረፍት —————-
ቀበና አንድ ወንድ ልጇን አጥታለች። ገዛኸኝ ፅዋመስቀል ዛሬ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አቶ ገዛኸኝ ፅዋመስቀል፣ በ1954 ዓ/ም በመጀመሪያ በግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በዚያን ጊዜ አጠራር ልዩ ካቢኔ (ኤታማዦር) ውስጥ በሬዲዮ ኦፕሬተርነት አገልግሏል። በሗላም ወደ ማስታወቂያ ሚኒስተር መ/ቤት ተዛውሮ አገሩንና ሕዝቡን በጋዜጠኝነት የሞያ ዘርፍ ያገለገለ ከመሆኑም በላይ፣ እንዲሁም በቪኦኤ (VOA) በአማርኛ ዜና ላይ የተለያዩ የስፖርት ነክ እርእሶች የሚዘግብ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነበረ። በመካከሉም በደርግ ዘመነ መንግሥት ለሰሜኑ ጦርነት የግዳጅ ክተት አዋጅ ሲታወጅ ባለው የጋዜጠኝነት ሞያ ከአባት ጦር ጋር አብሮ በመዝመት ግዳጁን የተወጣ ወንድማችን ነበር። ገዛኸኝ ፅዋመስቀል በቀበና ኮርያ ሰፈር ከ50 አመት በላይ ትዳር ይዞ ልጆች ወልዶ የኖረና ሠፈሩን የሚወድ ፣ በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎትና በመረዳጃ እድር እንዲሁም በአሁኑ ወቅት እየተገነባ ባለው የጤና ጣቢያ አገልግሎት መስጫ አካል ለሆነው ለይቶ ማቆያን ግንባታን ከሚያስተባብሩና በሞያው ሥነፁሁፍና በተለያዩ እርእሶች ላይ ስለ ቀበና ፅሁፍ በማዘጋጀት ላይ የነበረ ወንድማችን ነበር። ገዛኸኝ ፅዋመስቀል ከሁሉ የቀበና ነዋሪ ጋር ተግባቢ ፣ትንሸ ትልቁን አክባሪ፣ ከሥራ ባልደረቦቹ ጋር ተግባቢ ከራሱ ይልቅ ለአገሩና ለህዝብ ቅድሚያ የሚሰጥ ትልቅ ሰው ነበር። የወንደማችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን። ለባለቤቱ ፣ለልጆቹ ፣ ለመላ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን አሜን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና አንድ ውድ ልጇን በድንገት አጣች።ብርሃኑ ኣለማየው በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል። ብርሃኑ በሳውዝ ኣፍሪካ ወንበዴዎች ዘራፊዎች ታጣቂ መሳሪያ በያዙ ተመቶ ህይውቱ ኣልፎል ብርሽ ትልቅ ትንሽ የማይል ሰው ኣክባሪ ሰው ወዳድ እንዲሁም ለሁሉም የሰፈር ልጅ ደራሽ ከሁሉ ጋር ተመሳስሎ የሚኖር ምርጥ ልጅ ነበርለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለጎደኞቹ ሁሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር መፅናናትን ይስጥልን ኣሜን: : በድንገት ላጣነው ወንድማችን ፈጣሪ እግዚአብሔር ነብሱን በገነት ያሳርፍልን:: ኣሜን:: ለወንድም እህቶቹ፣ ዘመድ ወዳጆቹ እንዲሁም አብሮአደግ ጓደኞቹ ፈጣሪ አምላክ መፅናናትን ይስጥ። የወንድማችንን ነፍስ በሰላም ከደጋጎቹ ጎን ያሳርፍልን። አሜን
ዜና እረፍት ቀበና ወጣትና ውድ ልጇን አጣች። ኣብይ ዳምጠው በድንገት በሚኖርበት በሳውዝ ኣፍሪካ ከተማ ይኖር ነብር ባደረበት ትንሽ ጊዜ ህመም ባለመዳኑ ህይወቱ ኣልፎል ኣብይ ዳምጠው ኮርያ ሰፈር ተወልዶ ያደገና ለቁምነገር ከበቁ ወጣቶች አንዱ ነበር። ኣብይ ዳምጠው ትሁት ፣ትንሽ ትልቁን አክባሪ ፣ እንደነበር ሁሉ ይመሰክራል እንዲሁም ለሁሉ ተላላኪ ታዛዥ ደግ ወጣት ነበር ለወንድሞቹ ለህቱ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመድ ለጓደኞቹ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን አሜን። በድንገት ላጣነውም ወንድማችን ፈጠሪ እግዚአብሄር ነፍሱን በገነት ከአባቱ ከእናቱና ከደጋግ ወንድሞቹና እህቶቹ ጎን ያሥርፍልን። አሜን።
ዜና ዕረፍት ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን በድንገት አጣች። ተወልዶ ባደገበት ቀበና ኮሪያ ሠፈር 'ሶኔ' በሚል ቅጽል ስም የሚታወቀው ደረጀ ገመቹ ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ/ም በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል። ሶኒ ገመቹ በአስተማሪነት ለረጅም ዓመታት የሰራና ሃገሩንና ህዝቡን በቅንነት ያገለገለ ሲሆን፤ ከሥራ ባልደረቦቹ፣ ከወዳጅ ዘመዶቹና ከጓደኞቹ ጋር ተግባቢ፤ ትንሽ ትልቁንም አክባሪና ትሁት ሰው ነበር። ሶኒ በሰፈር ውስጥ የጎደኞቹንና የአብሮአደጎቹን ጉሩፕ በመምራት እንዲሁም በቀልደኝነቱ ይታወቅ ነበር። የውድ ወንድማችን የቀብር ስነስርዓት ዛሬ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ/ም ተፈፅሟል። ፈጣሪ እግዚአብሔር ነፈሱን በገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹም መፅናናትን እንዲሰጥ እንለምናለን። አሜን።
ዜና ዕረፍት ቀበና አንድ ውድ ልጇን በድንገት አጣች። ተሾመ ግርማ በቅፅል ስሙ (ጭሎ ግርማ) በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል። ተሾመ ግርማ በልጅነቱ አባቱ ለሀገራቸው ለዉድ ኢትዮጵያ በከፈሉት የህይወት መሰዋዕትነት በኩባ ሪፐብሊክ የትምህርት ዕድል አግኝቶ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት አጠናቆ ወደሚወዳት እናት ሃገሩ በመመለስ በተለያዩ ቦታዎች እናት ሃገሩን በቅንነት አገልግሏል። ለናት ሀገራቸው ከብር የተሰውትን ጀግኖች በየአመቱ የሚደረገውን መታሰቢያ ከሚያስተባቡሩት አንዱ ነበር። ተሾመ ግርማ ከዘመዶቹና ከአብሮአደግ ጓደኞቹ ጋር ተግባቢ፤ ትንሽ ትልቁንም አክባሪና ትሁት ሰው ነበር። የውድ ወንድማችን የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ/ም ተፈፅሟል። ለወንድም እህቶቹ፣ ዘመድ ወዳጆቹ እንዲሁም አብሮአደግ ጓደኞቹ ፈጣሪ አምላክ መፅናናትን ይስጥ። የወንድማችንን ነፍስ በሰላም ከደጋጎቹ ጎን ያሳርፍልን። አሜን
ዜና እረፍት ቀበና ወጣትና ውድ ልጇን አጣች። ቴዎድሮስ ተፈራ (እያዩ) በድንገት በሚኖርበት በለንደን ከተማ ባለቤቱና አንድ ልጁ እና እህቱ ብርሀኔ ተፈራ ለእረፍት አዲስ አበባ በሄዱበት ወቅት ውድ ወንድማችን እቤቱ ውስጥ ህይወቱ አልፎ ተገኝቶል። እያዩ በቀበና ኮርያ ሰፈር ተወልዶ ያደገና ለቁምነገር ከበቁ ወጣቶች አንዱ ነበር። እያዩ ትሁት ፣ትንሽ ትልቁን አክባሪ ፣ ለንደን የሚገኝውን የቀበና ኮርያ ሰፈር አብሮ አደጎች ማህበር ከሚያስተባቡሩት ውስጥ አንዱ የነበር እንዲሁም በተለያየ የማህረሰብ አገልግሎት በለንደን በሚገኝውን ቤተክርስቲያን በቅንነት የሚያገለግል ብርቅየ ወጣት ነበር። ለባለቤቱ ፣ለልጁ ፣ ለእህቱ ለብርሀኔ ተፈራ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመድ ለጓደኞቹ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን አሜን። በድንገት ላጣነውም ወንድማችን ፈጠሪ እግዚአብሄር ነፍሱን በገነት ከአባቱ ከእናቱና ከደጋግ ወንድሞቹና እህቶቹ ጎን ያሥርፍልን። አሜን።
እጅግ በጣም የሚያሳዝን ዜና ነው።
መካሪዎች፣ አስታራቂዎች፤ ታሪክ መስካሪዎችና አስተማሪዎቻችን የነበሩትን አዛውንት እናት አባቶቻችንን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ እያጣን ነው። ያሳዝናል። ኮሎኔል አሰፋ ዕድሜአቸውን ሙሉ ሃግራቸውንና ህዝባችውን በጀግንነትና በታማኝነት ያገለገሉ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ለቀበና ኮሪያ ሠፈር ልማትና ዕድገትም ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ እድሚያቸውን ሙሉ ታግለዋል፤ አገልግለዋል። ለዚህም ታሪክ ሲዘክራቸው ይኖራል። በተጨማሪም ከሽማግሌው ጋር ሽማግሌ፣ ከወጣቱ ጋር ደግሞ ወጣት በመሆን ሁሉንም በፍቅርና በአክብሮት ያስተናግዱ የነበሩ ውድ አባት ነበሩ።
አግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። መላ ቤተሰቡንም ያጽናናልን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ውድ ልጇን አጣች። ውድ ወንድማችን አቶ ዘሪሁን ደስታ (የነ መለሰ ተፈሪ ወንድም) ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ባለፈው እሁድ (March 13, 2022) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ረቡዕ (March 16, 2022, 10Am to 11Am) በ አትላንታ ቅድስት ማርያም ካቴድራል የፍትሐት ስነስርዓት ተደርጎ በ 12pm የቀብሩ ስነስርዓት በዚሁ በ አትላንታ
ይጠናቀቃል ።አቶ ዘሪሁን ከትልቅ ከትንሹ ጋር በቀላሉ መግባባት የሚችል፣ ሰው አክባሪ፣ ተጫዋችና ሰላምተኛ ሰው ነበር።
ቸሩ ፈጣሪ የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡ፣ ጓደኞቹና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ያድልልን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን አጣች። ውዱ ወንድማችን ረድኤት ተረፈ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንትና፣ ሰኞ፣ ሚያዝያ 17 ቀን፣ 2014 ዓ/ም (April 25, 2022) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቀብሩ ስነስርዓትም ዛሬ፣ ሚያዝያ 18 ቀን ተፈጽሟል።ረድኤት እጅግ በጣም ትሁት፣ ትልቅ ትንሹን አክባሪ፣ ከሁሉም ተግባቢ፤ አስተዋይና ቅን የሆነ የቀበና ፈርጥ ነበር።ቸሩ ፈጣሪ የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ መፅናናትን ያድልልን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና አንድ ውድ ልጇን በድንገት አጣች።
ውድ ወንድማችን ወንድሙ ገብረ ሥላሴ በደረሰበት ድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ሰኞ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ/ም (January 17, 2022) ይኖርበት በነበረው ሃገር አሜሪካ፤ በዋሽንግተን ዲሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል።
ወንድሙ ገ/ሥላሴ ቀበና ካፈራቻቸው ደጋግ ሰዎች አንዱ ነበር።
ወንድሙ ገ/ሥላሴ ትምህርቱን ከአጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስትር ውስጥ በፊልም ቀረፃ እንደ ኢትዮጰደያ ዘመን አቆጣጠር ከ1975 -1983 ዓ/ም አገራቸውን በቅንነት ሲያገለግል ቆይቶ በተደረገው የመንግስት ለውጥ በፖለቲካ ውሳኔ መሠረት ከስራ እንዲሰናበቱ ተደርጓል።
እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2010 በአሜሪካ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቶ ከመጣ በኋላ በዳላስ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ ABM company ለ11 ዓመታት በቅንነትና በታማኝነት አገልግሏል። ወንድሙ በሠራባቸውና በኖረባቸው ቦታዎች ሁሉ ከሥራ ባልደረቦቹ፣ ከወዳጅ ዘመዶቹና ከጓደኞቹ ጋር ተግባቢ፤ ትንሽ ትልቁንም አክባሪና ትሁት ሰው ነበር። የወድ ወንድማችን እስከሬን የሚያርፈው በውድ ሃገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ ሐሙስ ጥር 19፣ 2014 ዓ/ም (January 27, 2022) በዲሲ በቅድስት ማሪያም ቤተክርስትያን ከጠዋቱ 10 :00 Am ጀምሮ የፀሎትና ፍታት ስርዓት ተድርጎ ስለሚሸኝ የምትችሉ ሁሉ መጥታችሁ የፀሎት ሰርዓቱን መካፈልና ሽኝት ማድርግ ትችላላችሁ። ፈጣሪ እግዚአብሔር ነፈሱን በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹም መፅናናትን እንዲሰጥን እንለምናለን። አሜን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን አጣች። ውዷ እህታችን ዶክተር መለሰች የማነ (የነበረካ ታላቅ እህት) ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታናለች። የቀብሯ ስነስርዓትም ዛሬ ጥር 1 ቀን 2014 ዓ/ም ተፈጽሟል።
ዶ/ር መለሰች በወጣትነቷ በጣም ጎበዝ ተማሪ የነበረች ከመሆኗም በላይ ለብዙዎችም አርአያ የሆነች ትጉህ ተማሪ ነበረች። ባመጣችውም አኩሪ ውጤት ምክንያት ወደ ቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት በመሄድ የህክምና ትምህርቷን አጠናቃ ወደ ውድ ሃገሯ በመመለስ ሃገሯንና ህዝቧን ለረጅም ዓመታት በቅንነት አገልግላለች። ዶ/ር መለስች ከትልቅ ከትንሹ ጋር በቀላሉ መግባባት የምትችል፣ ሰላምተኛ፣ በጣም ትሁትና በመላው ቀበና የምትታወቅ የቀበና ምርጥ ልጅ ነበረች።
ቸሩ ፈጣሪ የውድ እህታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቧ፣ ወዳጆቿና ጓደኞቿ ሁሉ መፅናናትን ያድልልን።
ቀበና ሌላ ልጇን አጣች
ውድ እህታችን እልፍነሽ ቢተው ባደረባት ህመም ምክንያት ለረጅም ግዜ በህክምና ስትረዳ ቆይታ ዕሮብ ህዳር 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታናለች።እልፍነሽ በዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ዘርፍ ለረጅም ዓመታት የሠራች ሲሆን ሃገሯንና ወገኗንም በቅንንነት አገልግላለች።እልፍነሽ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፣ ትሁትና ከሁሉም ጋር ተግባቢ ቁምነገረኛ በሙያዋ የተቸገሩትን ትረዳ የነበረች ቀልደኛና ተጨዋች ውድ እህታችን ነበረች ።ፈጠሪ እግዚአብሔር የእህታችንን ነፍስ ይማርልን። በአጸደ ገነትም ያኑርልን። እንዲሁም ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቿ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን። አሜን
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ልጇን አጣች
በቀድሞው የኦሜድላ (የፖሊስ) ሰራዊት ውስጥ የቦክሰ ሰፖርተኛ የነበረው፣ ሃገሩን ወክሎ በተለያዩ ሃገራት የተወዳደረውና በቀድሞው ምሰራቅ ጀርመን የቦክስ ስፖርት ስልጠና በመከታትል ሃገር ውሰጥ እስከ ብሔራዊ ቡደን ድረስ ያሰለጠነው ውዱ ወንድማችን ኢንስፔክተር ደምሴ ካሣ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ/ም ከዚህች ዓለም በሞት ተለይቷል። ደምሴ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፣ ትሁትና ከሁሉም ጋር ተግባቢ ሰው ነበር። ፈጠሪ እግዚአብሄር የወንማችንን ነፍስ ይማርልን፣ በአጸደ ገነትም ያኑርልን። እንዲሁም ለመላው ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን። አሜን
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን አጣች። ውዱ ወንድማችን ሞገስ ግዛው ባደረበት ህመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንትና፣ ሐሙስ፣ ነሐሴ 20 ቀን፣ 2013 ዓ/ም (August 26, 2021) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቀብሩ ስነስርዓትም ዛሬ፣ ነሐሴ 21 ቀን ተፈጽሟል።ሞገስ እጅግ በጣም ትሁት፣ ትልቅ ትንሹን አክባሪና ከሁሉም ተግባቢ ነበር። ለበርካታ ዓመታትም በግል ኦዲተርነት ሃገሩንና ህዝቡን በቅንነት ያገለገለ ምርጥ የቀበና ልጅ ነበር።ቸሩ ፈጣሪ የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ መፅናናትን ያድልልን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና አንድ ውድ ልጇን በድንገት አጣች።
ውድ ወንድማችን ዳንኤል ጉቱ በደረሰበት ድንገተኛ ህመም ምክንያት በትናንትናው ዕለት ሐምሌ 21 ቀን 2013 ዓ/ም ይኖርበት በነበረው ሃገር ቶሮንቶ፤ ካናዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቶናል።
ዳንኤል ጉቱ ቀበና ካፈራቻቸው የቦክስ አስፖርተኞች አንዱና፣ ሃገራችንን ኢትዮጵያን በመወከል በተለያዩ ሃገራት የተወዳደረ ምርጥ ቦክሰኛ ነበር። የቦክሰኝነት ስልጠናም በውጭ ሃገር ወስዶ በሃገር ውሰጥ ያሰለጥን ነበረ። በህዝብ ማመላለሻ ድርጅት ውስጥም የስምሪት ክፍል ሀላፊ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን በሠራባቸውና በኖረባቸው ቦታዎች ሁሉ ከባልደረቦቹ፣ ከወዳጅ ዘመዶቹና ከጓደኞቹ ጋር ተግባቢ፤ ትንሽ ትልቁንም አክባሪና ትሁት ሰው ነበር።
ፈጣሪ እግዚአብሔር ነፈሱን በገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹም መፅናናትን እንዲሰጥን እንለምናለን። አሜን።
ዜና እረፍት
ቀበና ዛሬም አንድ ውድ ልጇን በድንገት አጣች ።
ውዱ ወንድማችን ኢንጂነር ሚካኤል ገሠሠ ከዚህች ዓለም በሞት ተለይቶናል።
ሚኪ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በሕብረት ፍሬ ት/ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በ1970 ዓ/ም ለጀግኖች ልጆች በተሠጠው ነፃ የትምህርት ዕድል መሠረት ወደ ኪውባ በመሄድ በወጣቶች ደሴት በESBEC #43 መንግስቱ ኃይለማርያም ት/ቤት ከ6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ተምሯል።
ከዚያም በማታንዛስ ዩኒቨርሰቲ በአግሮ ኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ በማስተርስ ዲግሪ በ1990 ዓ.ም ከተመረቀ በኋላ ወደ ውድ ሃገሩ በመመለስ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች እናት ሃገሩን በቅንነትና በታማኝነት አገልግሏል።
በመጨረሻም በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በባዮፊዩል ኢንጂነሪንግ ዴቨሎፕመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን በሀላፊነት በማገልገል ላይ እንዳለ ሰኞ ጥዋት (መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም) በድንገት ህይወቱ አልፏል::ሚኪ በተወለደበት ሠፈር በቀበና እንዲሁም በመላው የኢትዮኪውባ ተማሪዎች ተወዳጅና ተግባቢ፤ ትንሽ ትልቁን አክባሪ ወንድማችን የነበረ ሲሆን በተለያዩ የማኅበራት አንቅስቃሴዎች ጉልበቱን፣ ዕውቀቱንና ገንዘቡን ያለምንም ስስት በመለገሥ ከመላው ቤተሠቦቹ ጋር ተሳታፊ ነበር::በውድ ወንድማችን ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሠማንን መሪር ሀዘን እየገለፅን የቀብሩ ሥነሥርዓት ዛሬ መስከረም 26/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:00-9:00 ሰዓት በፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ተፍፅሟል::ለእናቱ እማሆይ እታገኝ ዘመድኩን፣ ለባለቤቱና ለልጆቹ ፣ ለእህቶቹ ለዶክተር ሙሉዓምና ለፀሐይ ገሠሠ ፣ ለወንድሞቹ እንዲሁመ ለመላው ወዳጅ ዘመድና ጓደኞቹ መፅናናትን እየተመኘን ፈጣሪያችን እግዚአብሄር የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን እንማፀናለን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን አጣች። ውዱ ወንድማችን ዳንኤል ከበደ ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንትና፣ ሰኞ፣ ግንቦት 2 ቀን፣ 2013 ዓ/ም (May 10, 2021) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቀብሩ ስነስርዓትም ዛሬ፣ ግንቦት 3 ቀን ተፈጽሟል። ዳንኤል እጅግ በጣም ትሁት፣ ትልቅ ትንሹን አክባሪና ከሁሉም ተግባቢ፣ የመጨረሻ ደግ፣ ለሰፈሩ ለቀበና ልጆች ተሟጋችና ሟች፣ ለሁሉም ፈጥኖ የሚደርስ በመላው ቀበና የሚታወቅ የሰፈራችን ፈርጥና ጀግና ነበር። ዳንኤል ክብር ዘበኛን ጨምሮ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሃገሩንና ወገኑን ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይል ለረጅም ዓመታት አገልግሏል። ቸሩ ፈጣሪ የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡም መፅናናትን ያድልልን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ውድ ልጇን አጣች። ውድ ወንድማችን ንጉሱ ተፈሪ (የነ መለሰ ተፈሪ ወንድም) ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ (March 30, 2021) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቀብሩ ስነስርዓትም በማግስቱ ረቡዕ (March 31, 2021) ተፈጽሟል። ንጉሱ ከትልቅ ከትንሹ ጋር በቀላሉ መግባባት የሚችል፣ ሰው አክባሪ፣ ተጫዋችና ሰላምተኛ ሰው ነበር።
ቸሩ ፈጣሪ የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡ፣ ጓደኞቹና ወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ያድልንን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና አንድ ውድ ልጇን በድንገት አጣችጌታቸው ውብሸት በድንገት ሐምሌ 9/ 2013 ዓ/ም አርፏል።
ጌታቸው በትምህርት ሚኒሰተር ስር በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በአስተማሪነትና በአስተዳደር ለረጅም ዓመታት ያገለገለ ሲሆን፤ ከሥራ ባልደረቦቹ፣ ከወዳጅ ዘመዶቹና ከጓደኞቹ ጋር ተግባቢ፤ ትንሽ ትልቁንም አክባሪና ትሁት ሰው ነበር። ጌታቸው ውብሸት በቀበና ኮርያ ሠፈር የተለያዩ የበጎ አደራጎት ሥራዎችን በመስራት የትውልድ ሰፈሩን በቅንነት ያገለግል ቅን ሰው ነበር። የውድ ወንድማችን የቀብር ስነስርዓት ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓ/ም ተፈፅሟል።
ፈጣሪ እግዚአብሔር የወንድማችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹም መፅናናትን እንዲሰጥ እንለምናለን። አሜን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና በዛሬው ዕለት አንድ ውድ እናቷን አጥታለች። እናታችን እማሆይ አበራሽ አጠና (የነዮሐንስ ገ/ሥላሴ) እናት ባአደረባቸው ህመም ምክንያት በዛሬው ዕለት መጋቢት 13 ቀን፣ 2013 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እናታችን እማሆይ አበራሽ የኛን የሰው ልጆችን ሃጢያት አስቀድመው ተገንዝበው ፈጣሪ አምላካችን ኢትዮጵያ ሃገራችንን እንዲታደግና ህዝቧንም ይቅር ይል ዘንድ በዘወትር ጸሎታቸው የሚለምኑ ትሁት፣ ትንሽ ትልቁን አክባሪና ሰላምተኛ እናት ነበሩ። የእማሆይ እአበራሽ አጠና የቀብር ስነስርዓት በነገው ዕለት በቀበና መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል። ፈጠሪ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን።
ለልጇቻቸው ለወንድሙ ገ/ሥላሴ፣ ለዓለም ገ/ሥላሴ፣ ለዮሐንስ ገ/ሥላሴ፣ ለአበበ ገ/ሥላሴ እንዲሁመ ለመላው ቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ፈጠሪ እግዚአብሄር መፅናናትን ይስጥልን። አሜን።
ዜና ዕረፍት
ኖርዝ ካሮላይና (North Carolina) የሚኖረው የውድ ወንድማችን የደረጀ ዘውዱ ልጅ ሩት ደረጀ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ትናንት የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም (February 15, 2021) በተወለደች በ19 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታናለች።
ሩት አዲስ አበባ የተወለደች ሲሆን እነደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2004 ዓ/ም ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አሜሪካ በመምጣት በኖርዝ ካሮላይና ግዛት ትኖር ነበር። በአጭሩ የተቀጨችው ሩት ሩቅ ግብና ትልቅ ራዕይ የነበራት ትጉህ ተማሪ ነበረች። የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ከማጠናቀቋም በላይ የኮሌጅ ምዝገባ ጨርሳ ትምህርት ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ ነበረች።
የቀብሯ ስነስርዓት የሚፈጸመው ቅዳሜ ፣ የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ/ም (February 20, 2021) ነው።
ለቀብር ስነስርዓቱ ማስፈጸሚያ ይረዳ ዘንድ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ማሰባሰብ ስለጀመሩ መርዳት የምትሹ በካሽ አፕ (Cash App) ለዶክተር ቢኒያም ሙሉነህ (Benyam Muluneh) መላክ የምትችሉ ሲሆን፤ በዜል (Zelle) መላክ የምትሹ ደግሞ የዶክተር ቢኒያም ሙሉነህን ስልክ ቁጥር (703-915-4836) በመጠቀም መላክ ትችላላችሁ።
ደረጀንና ቤተሰቡን በስልክ ማጽናናት ለምትሹ ስልክ ቁጥሩ 984-439-4442 ነው።
ፈጣሪ የልጃችንን ነፍስ ይማርልን። በአጸደ ገነትም ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቧም መፅናናትን ያድልልን።
የእናታችን ወ\ሮ ብሪቱ ሄይ (የአዳኑ እናት)ነፍስ በአጸደገነት ያኑርልን ለመላው ቤተሰብ መጽናናት እንመኛለን
ወ/ሮ ብሪቱ ሄይ (የነአዳኑ እናት) ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዝያ 27 ቀን 2013 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተውናል። የቀብራቸው ስነስርዓትም በዛሬው ዕለት (ሚያዝያ 28 ቀን) ተፈፅሟል::
እናታችን በጣም ትሁት፣ ትንሽ ትልቁን አክባሪ፣ ሰላምተኛና ለሰው አዛኝ ነበሩ :: ይህን መልካም ባህሪያቸውንም ለልጆቻቸው አስተምረው አልፈዋል::
ፈጣሪ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማርልን። ለመላ ቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመድ ሁሉ መፅናናትን ይስጥልን። አሜን።
ቀበና አንድ ውድ ልጇን በድንገት አጣች።
ጌታቸው ታምሩ (የጋሽ ታምሩ ዮሴፍ ልጅ) በሥራ ላይ እያለ በድንገት ትናንት፣ መጋቢት 1 ቀን 2013 ዓ/ም አርፏል።
ጌታቸው በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በጅማ ለረጅም ዓመታት የሰራ ሲሆን፤ ከሥራ ባልደረቦቹ፣ ከወዳጅ ዘመዶቹና ከጓደኞቹ ጋር ተግባቢ፤ ትንሽ ትልቁንም አክባሪና ትሁት ሰው ነበር።
ጌታቸው ታምሩ ለዛ ባላቸው ቀልዱ ከመታወቁ ባሻገር፤ የተለየ የአነጋገር ዘይቤና ተሰጥዖ ያለው ሰው ነበር።
የውድ ወንድማችን የቀብር ስነስርዓት ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ/ም ተፈፅሟል።
ፈጣሪ እግዚአብሔር ነፈሱን በገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡና ወዳጅ ዘመዶቹም መፅናናትን እንዲሰጥ እንለምናለን። አሜን።
ፈጣሪ የውድ ወንድማችንን ነፍስ ይማርልን። በአጸደ ገነትም ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡ፣ ወዳጆቹና ጓደኞቹም መፅናናትን ያድልልን።
የእናታችንን እትዬ እጅጋየሁን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን ለመላው ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን
የእታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡም መፅናናትን ያድልልን።
ዜና ዕረፍት
ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን አጣች። ውዷ እህታችን ፍሬህይወት ደመላሽ ባደረባት ህመም ምክንያት በህክምና ስትረዳ ቆይታ ሐሙስ (September 03) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። የፍትሃቷ ስነስርዓትም በዛሬው ዕለት በዋሺንግተን ዲሲ ደብረኃይል ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተፈጸመ ሲሆን፤ የቀብሯ ስነስርዓት ደግሞ በዛሬው ዕለት (September 05) ከቀኑ 1:00 - 1:30 PM በHeritage Memorial Cemetery
13472 Poplar Hill Rd, Waldorf MD 20601 ይፈፅማል።
ፍሬህይወት እጅግ በጣም ትሁትና በመልካም ስነምግባሯ በመላው ቀበና የምትታወቅ የቀበና ምርጥ ልጅ ነበረች።
ቸሩ ፈጣሪ የእህታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቧም መፅናናትን ያድልልን።
የአባታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን ለመላው ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን
ዜና ዕረፍት
የ ሀምሳ አለቃ አለባቸው ሞላ በአደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ቅዳሜ October 31, 2020) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ስነስራታቸውም በዛሬው እለት በደብረ ሊባኖስ ተፈጽሞል ::
አባታችን አገራቸውን በፖሊስ ሰራዊት ውስጥ ለእርጅም አመት በጡረታ እስቲገለሉ ድረስ በቅንነት አገልግለዋል ::
የሀምሳ አለቃ አለባቸው ትልቅ ትንሹን አክባሪ ፣ ሰላምተኛና የአምስት ልጆች አባት ነበሩ::
ቸሩ ፈጣሪ የአባታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። በሰሜን አሜሪካ ለሚኖሩት ለሁለት ልጆቻቸውና ቀበና ለሚኖሩት ለ3 ልጆቻቸው እንዲሁም ለመላ ቤተሰቧቻቸው ፣ ወዳጆቾቸውና ጓደኞቾቸው መፅናናትን ያድልንን።
የ አባታችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡም መፅናናትን ያድልልን።
በጣም ኣሳዛኝ ዜና
ዕድሜአቸውን ሙሉ ሃገራቸውንና ህዝባችውን በጀግንነትና በታማኝነት ያገለገሉት ውድ አባታችን መጋቢ አስፋው አበበ (የቀበና አብሮአደግ ማኅበራችን አስተባባሪ ኮሚቴና የዚህ ስብስብ መሥራች ከሆኑት አንዱ የሆነው የሰለሞን አስፋው አባት) በዛሬው ዕለት በተወለዱ በዘጠና ሰባት (97) ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። መጋቢ አስፋው ከሽማግሌው ጋር ሽማግሌ፣ ከወጣቱ ጋር ወጣት በመሆን ሁሉንም በፍቅርና በአክብሮት ያስተናግዱ የነበሩ በተለይም ደግሞ በግምት የዛሬ አርባ (40) ዓመት አካባቢ የቀበና እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ወጣቶች ለዴሞክራሲና ለነፃነት ባደረጉት ተጋድሎ ላይ በቀጥታ የተሳተፉና ትግሉንም በይፋ የተቀላቀሉ ቆራጥ አባታችን ነበሩ። የመልካም አባትነትና የንጹህ ኢትዮጲያዊነት ዓርዓያነታቸው ትውልድ ተሻጋሪ ነው።
አግዚአብሔር ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። ቤተሰቡንም ያጽናናልን።
የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡም መፅናናትን ያድልልን።
ቀበና ሌላ ብርቅዬ ልጇን አጣች። ውዱ ወንድማችን ግርማ ኃይሉ (የነ ሙሉጌታ ኃይሉ ወንድም) ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ሰኞ፣ ሐምሌ ፮ ቀን (July 13th) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። የቀብሩ ስነስርዓትም በትናንትናው ዕለት ተፈጽሟል። ግርማ እጅግ በጣም ትሁትና በመልካም ስነምግባሩ እንዲሁም በልዩ የእግር ኳስ ችሎታው በመላው ቀበና የሚታወቅ ብርቅ የሰፈራችን፣ የቀበናችን ፈርጥ ነበር። ቸሩ ፈጣሪ የወንድማችንን ነፍስ በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለመላ ቤተሰቡም መፅናናትን ያድልልን።
[ እጅግ በጣም የሚያስደስት ዜና ነው። የሚልሱት የሚቀምሱት ለሌላቸው ወገኖቻችን ከመድረስ የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገር አለ? ልብ ላለ ሰው እኮ፣ በዚህች ምድር ላይ ጥረን ተጣጥረን ያፈራነው ንብረትም ሆነ ገንዘብ ተከትሎን አይሄድም። እንዲህ ያለው መልም ሥራ ግን መከተል ሳይሆን ቀድሞ ነው የሚጠብቀን። ልብ ያለው ልብ ይበል። ] !!!!!!!!!!!!! [[ ይኽ መልካም ጅማሬና መሰረት የጣለ ፕሮጀክት ላይ ዜናውን ከሩቅ ሆኘ ከመስማት ይልቅ ዕድል አግኝቸ እነ አኔ በ እናንተም መረጃውን ልካችሁ በጥቂቱ እንድሳተፍ በመቻሌ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ብዙ የሰፈር ጀግናና ጨዋ አባቶችን እናትችን ጎበዝ ጎበዝ ወጣቶችን ስላየሁ ደስ ብሎኛል!:: አሁንም ገና ብዙ ለመስራትና ለማድረግ ዕድል ተከፈተ እንጂ ብዙ ይቀራል እናም እግዚአብሔር ይርዳን ሁሉ በፍጥነት ይከናወን ዘንድ ምኞቴ ነው በየጊዝው መረጃ ለምታቀብሉን ታላቅ ምስጋና አለኝ በርቱ!!!ስለ ጅማሮው ትልቅ ስኬት ነውና ]]
ከቀበና አብሮ አደጎች አስተባባሪዎች የቀረበ መልእክት
ዜና ዕረፍት - መላ ዓለምን እያስጨነቀ ያለው ቀሳፊ ተስቦ የራሳችንንና ብርቅዬ ወንድማችንን አሸናፊ ተፈራን በትላንትናው ዕለት (April 4th, 2020) ነጥቆናል። አሸናፊ ከሁለት ሳምንት በላይ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ በሚገኘው አድቬንቲስት ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ነው ያረፈው። ወዱ ወንድማችን አሸናፊ ለሰው ታላቅ አክብሮት የነበረው፤ ጓደኞቹን የሚያፈቅር፤ ትልቅ ትንሽ ሳይል ሁሉን የሚያከብር፣ ትሁት፣ ለወገኑ ለሃገሩና ለቆመለት ዓላማ ሁሉ ያለማመንታት በቆራጥነት በመቆም የሚታወቅ ጀግና ኢትዮጲያዊ ነበር። አሸናፊ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበር። ቀብሩ የሚፈጸምበት ቀንና ቦታ በአሁኑ ሰዓት በውል ያልታወቀ ሲሆን፤ በዚሁ ቀሳፊ ወረርሺኝ ምክንያት ከተወሰነ ሰው በላይ መሰባሰብ ስለማይቻል፣ የቀብሩ ስነስርዓት ሊፈጸም የሚችለውም በጣም በተወሰኑ ሰዎች ብቻ ይሆናል። የቀበና አብሮ አደጎች ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ ከተለያዩ አባላቶቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል። አብዛኛው ሰው የሚጠይቀው እንዴት አድርገን የአሸናፊን ቤተሰብ በዚህ ጭንቅ ሰዓት መርዳት እንደሚገባን ወይም እንደምንችል ነው። እስካሁን አብዛኞቻችሁ አይታችኋል ብለን እንደምንገምተው፣ ለቀብር ሰንስርዓቱና ቤተሰቡንም ለመርዳት የ ጎ ፈንድ ሚ (gofundme) አካውንት ተከፍቶ ገንዘብ እየተሰባሰበ ይገኛል። አንደ ቀበና ልጅነት፣ እንደ አሸናፊ ወንድም እህትነት፣ እኛም በበኩላችን የአባላታችንን ጥያቄ አንተርሰን በማህበራችን ስም ገንዘብ አሰባስበን ለባለቤቱ ለመስጠት ወስነናል። በጎ ፈንድ ሚ (gofundme) እርዳታ ላደረጋችሁ በአሸናፊ ቤተሰብ ስም ታላቅ ምስጋና እያቀረብን፤ እስካሁን ያልረዳችሁና መርዳት የምትፈልጉ ከዛሬ (04/05/20) እስከ ሐሙስ (04/09/20) ባለው ጊዜ ውስጥ ለአጥናፉ በቀለ በአካል፣ በቼክ ወይም በካሽ አፕ በመጠቀም ዕርዳታ ማድረግ እንደምትችሉ አናሳውቃለን። ለበለጠ ጌታቸውና ለሊበን በንቲም ገንዘብ መስጠት ትችላላችሁ። በቼክ ለምትልኩ የአጥናፉ አድራሻ 1517 Hideaway Place Silver Spring, MD 20906 በካሽ አፕ (Cash App) ለአጥናፉ በቀለ ለምትልኩ Cash App አግዚአብሔር ለመላው ባተሰቡ፣ ለወዳጆቹንና ለቀበና ህዝብ መጽናናትን ይስጥልን። ነፍሱንም በአጸደ ገነት ያኑርልን። ለጥያቄ በ 301-928-5038 ይደውሉ
ለ ውድ ወንድማችን አሸናፊ ተፈራ ልዑል እግዚአብሔር ነፍሱን በገነት ያኑርልን ለመላው ቤተሰቡም መጽናናትን ይስጥልን
በእውነት ለምናገር ዛሬ ቀበና ትልቅ ልጁን አጣ ለማናችንም አሹ ትንሹ ወንድም ልጅ ወገን ሆኖ በዋሽንግተንና አካባቢው በማንነቱ እንደኮራ በኢትዮነት ሳይደራደር ያች ተወልዶ ያደገባትን ቀበናን እንደኮራባት ምንም በማንጠብቀው ግዜ እና አለም አስጨናቂ ሁኔታውስጥ ባለበት እኛም የምንወድህ የምናፈቅርህ የምንኮራብህ መሆኑ በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እንወዳለን በተለይ እንደ እናት ለምትወድህ እህትህ ብርሐኔ እና መላው ዘመድ ወገንህን መጽናናት ይስጥ አግዚአብሔር ነፍስህንአሽዬ በገነት ያኑር ቀበና እራሳችሁን ጠብቁ sty home safe
የእህታችን ነፍሷን በገነት ያኑርልን ለ ቤተሰቡ ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን ከ ቀበና አብሮአደጎች ማህበር አስተባባሪዎች
IN LOVING MEMORY
IN MEMORY OF ROSA DESTA
In Memory of Our Abroadeg Rosa
Desta Feb 1966 - Ma 21, 2013
Press for the link
Kebena Mehder Magazine 2014

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ -------> kebena magazine 2014_web
Kebena Mahder Magazine 2015
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ -------> Kebena Magazine 2015_web
Kebena Mahader Magazine 2016
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ -------> Kebena Magazine 2016
Kebena Magazine From Koria Sefer Brothers
ለማንበብ እዚህ ይጫኑ -------> Koria sefer magazine 2017kebena magazine
WELLCOME
እንኳን ደህና መጣችሁ የ ቀበና ስፈር ልጆች
This website will serve as our means of communication as we plan our 5 year yekebena sefer abroadegoch family reunion this August 4 weekend 2019, you can also look our photo gallery 2013, 2014, 2015,2016,2017,2018 reunion, in memory honoring and remembering our brothers, our kids photo gallery, image of memorable yekoria sefer lijoch. Please send us your memorable pictures as well comment about what you are up to.
2013 Kebena Family Reunion Pictures
2014 Kebena Family Reunion Pictures
Ye Kebena Sefer Abroadegoch የ ቀበና ሰፈር አብሮአደጎች
As you see us how exited we are to see all of you, ye kebena sefrer lijoch coming together one big family, your presence will surely be of great pleasure to us. Let us commit our self to rich out to all ye koria sefer lijoch, as we inherited a gift of love and kindness from our family, we can able to pass it to our children.
Dedicated Group
After more than thirty years living abroad, we are now able to find one another and able to share our childhood memories and friendship that we carry throughout adult life, our long life journey bring us this moment and time having this rare opportunity for us to remember and pay tribute to those whose life was cut short during unpleasant time of our past, even though we ware sadden with that dark period time of our life, our dear brothers and sisters they will live forever in our memories, at this moment of our life journey can able us every year a chance to teach and share our root in kebena koria sefer for our children to know where we their parent come from.
Event Opening Hour የ ድርጊቱ መክፈቻ ሳአት
SATURDAY JULY 29 , 2018 LOCATION POPLAR RUN CLUBHOUSE
13500 STARGAZER LN SILVERSPRING MD.20906
TIME FROM 4PM To 2AM TEL NO 301-928-5038 & 703-839-3950