About us

Social Media

Our life’s journey began where we all grew up in KEBENA KOREA SEFER in ADDIS ABABA, ETHIOPIA. We always cherish our childhood memories and friendships that we carry throughout adult life. All of us inherited from our family love and kindness. At this time we live in the USA, CANADA, LONDON and other places around the world. Even though we live our lives separately for long periods of time without seeing each other, still our families love burn in our hearts. In March 2013, single phone call ignited our secret desires until it warmed our hearts with our family’s love and kindness. That single phone call gave us our first excited moment of that year. All our KEBENA KOREA SEFER ABROADEGOCH family were present at the Family‘s reunion in July 6, 2013 in Baltimore Maryland. That day when we saw all YESEFER ABROADEGOCH together our hearts are filled with emotional, excitement until this day. This is our success story and the second Family reunion was held on July 5, 2014, at this moment it accompanied with the first Edition of KEBENA MAHADER MEGAZIN gathering . We are now preparing for our up-coming 2015 reunion in Silver Spring Maryland from July 3rd through July 5th. Our future plan is for all of us to get the gift of love and kindness from all of our families. It is our desire and goal to pass to our children the love and friendship we all share. We always want you to join us all, you all YE KEBENA KOREA SEFER LIJOCH bring us so much joy and happiness.

አዘጋጆች መልዕክት

 ቀበና ሲባል፣ ኮርያ ሠፈር ሲባል፣ ሸክላ ሜዳ ሲባል፣ ሚሽን ሰፈር ሲባል፣ ጃንሜዳ ሲባል፣ ሐኪም ሜዳ ሲባል ወይም ኖራ ሜዳ ሲባል ልቡ ወከክ የማይል፣ በትዝታ የማይነጉድ፣ ልዩ የደስታ ስሜትም የማይሰማው የቀቤ ልጅ የለም። ወደን አይደለም፤ ፈልገንም አይደለም። ከደማችንና ከስጋችን የተዋሃደ መቼም ሊወጣ ወይም ሊሰወር የማይችል ትዝታና ፍቅር ስላለን ነው ለሠፈራችን፣ ለዚያች እትብታችን ለተቀበረችበት ወይም ላደግንባት መንደራችን። ሠፈራችንን፣ ቀያችንን በጣም እንወዳለን፤ እኛምእንደዛው እንዋደዳለን። ድሮማ፣ ጥንትማ፣ እንዲህ እንደ ዛሬው በየአቅጣጫው ተበትነን፣በየመስመራችን ተጉዘን ሳንለያይ፣ ሳንራራቅ ከጧት እስከ ማታ እንደመንትያ ተጣብቀን ነበር የምንውለውና የምናመሸው ብለን ስለሠፈራችን ፍቅር እንዳንጽፍ ይሄ በመጽሔቱ ውስጥ በደንብ ተገልጿል። ያጋጣሚ ነገር ሆነና አብዛኛዎቻችን ከቀበና ርቀን፤ ከቀበና ተለይተን መኖሩን ከተያያዝነው ዘመናት ተቆጥረዋል። ደግሞ ይባስ ብሎ በርካታ ውድ እህት ወንድሞቻችን፣ እናት አባቶቻችንና አያት ቅድም አያቶቻችን ከዚህ ዓለም ትተውን ሄደዋል። እኛ ደግሞ በህይወት ያለነው በያለንበት ሆነን ቀበናን መናፈቃችን እርስ በርስም መፈላልጋችንን አላቆምንም። ለነገሩማ ጊዜ በረዘመ ቁጥር፣ ግንኙነት በላላ ቁጥር መረሳሳት ነበር ለወትሮው የሰው ልጅ እጣ ፋንታው። የኛ የቀቤዎች ታሪክ ግን ለየት ያለ ነው። መሠረቱ ጥንቱኑ ጠንካራ ነበርና ጊዜም ሆነ የቦታ ርቀት ለይቶ አለየንም። እንፈላለጋለን ለጉድ። ከሌላ ከማንም ጋር ልናነሳው የማንፈልገውን ያን የጥንት ትዝታ፣ ያን የጥንት ወግ የምንጋራው የቀቤ አብሮ አደግ እንፈልጋለን። አውጥተን ባንናገረው እንኳን ይህ ፍላጎታችን በውስጣችን ተቀብሮ ያምሰናል። ትልቅ የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማናል። ከቀቤ ልጅ ጋር፣ ከአብሮ አድግ ጋር፣ ከገበናችን ጋር ማውራት፣ መገናኘት፣ መጠያየቅ፣ አለሁልህ አለሁልሽ መባባል ያሻናል፣ ይጠማናል የሚለው ይሆን መጽሔቱ ውስጥ ያልገባው? የቀቤ ልጅ ሁሌም አብሮ አደጉን ሲሻ፣ አብሮ አደጉን ሲያስስ እንደሚኖር? ይሄ ይሆን እንዴ የጎደለው? የለም፣ የለም፣ በጭራሽ አይመስልም። ይሄ እንዴት ይዘነጋል። ኑሮና ብልሃቱ ወደ ዕለት ተዕለት ጉዳያችን እንድናተኩር፤ አፍንጫችን ስር ያለውን ብቻ እንድናይ አስገድዶናል። መነፋፈቃችንን፣ መፈላለጋችንን አውቀን እንዳላወቀ ወደጎን ገፋ ገፋ እያደረግን እራሳችንን እየሸሸግን ከራሳችንም እየተደበቅን አስርተ ዓመታቶች አስቆጠርን። ለሁሉም ጊዜ አለው ሆነና ነገሩ፤ ገፋ ገፋ እያደረግን ወደጎን ለረዥም ጊዜ ያቆየነው ጉዳይ ከዚህ በኋላማ ወዴትም ልትገፉኝ፣ ልታቆዩኝም አትችሉም ብሎ አይኑን አፍጦ፣ ጥርሱን አግጦ ሊፈትነን ተነሣ። ጊዜው ደረሰና። እናም ቀቤዎችም መልስ መስጠት እንዳለባቸው አወቁ። ቀኑ መድረሱንም ተረዱ። ቀስ በቀስ በጊዜ ብዛት ተለያይተው ተራርቀው የቀሩትን ያህል፤ ቀስ በቀስ፣ ጊዜ ወስደው ረጋ ብለው መሰባሰብን፣ መገናኘትን፣ መጠያየቅን መረጡ። ያለብዙ ትግልና ጉትጎታም የመጀመርያውን የቤተሰብ መገናኛ፣ መሰባሰቢያ ቀን አከበሩ። በአካል ተገናኝተው፣ ፊት ለፊት ተቀምጠው ለማውጋት በቁ ብለን እንኳን እንዳንጽፍ ይሄም ተብሏል። ህይወት እንደሆን አጭር ናት። በጣም አጭር። ልባችን እያሻው፣ ኑሮና ብልሃቱ ደግሞ ከወዲያ ወዲህ ንፋስ እንደመታው ዛፍ እያወላገደን፤ አፈር ፈጭተን፣ ጭቃ አቡክተን፣ ውሃ ተራጭተን እንደ አንድ እናት ልጆች ሆነን ተላልሰን ያደግነውን እህትና ወንድሞቻችንን እስከ መርሳት ሊያደርሰን ሲሞግተን የከረመው ይበቃዋል። አሁን ጊዜው ደርሷል። እንግዲህ የጥንት የጥዋቱን፣ የአንድ ቤተሰብነታችንን አድሰን፣ አጠናክረን መጠያየቅ፣ መገናኘት፣ መተሳሰብ እንደገና ጀምረናል። እግዚአብሔርም ይህን ቅን ሃሣብ፣ ይህን ከልብ የመነጨ ሃሣብ ይባርከዋል። የስብስቡ ዓላማም ተራርቀን፣ ተለያይተን እንዳንቀር፣ በደስታም ሆን በመከራ አይዞህ አይዞሽ እንድንባባል፣ ለልጆቻችንም ታሪካችንን፣ እድገታችንን እንድናሳውቅ፣ እንድናስተላልፍ፣ የነሱም ታሪክ ስለሆነ እንድናስተምር፣ በዓመት አንድ ግዜም በአካል ተገናኝተን ለማውጋት፣ ለመወያየት፤ በቃ፤ ይህ ነው ዓላማው

 

July 20, 2014 160 - Copy