Our main purpose when we started all ye kebena sefer abroadegoch family reunion, we commit our self three years ago, a means for all ye kebena family to keep in touch with one another. This is especially important all our family spread across the US, or even the globe, In such a case we see each other once a year to celebrate new baby arrival, introduce all our kids one another, families to catch up where we left off our sefer memory, when we meet up with our abroadegoch after a long time-years even-it’s like no time has passed at all, our talk is non-stop because there is so much to catching up to do, and often to have a memorable event for years to come. Always to remember our kebena sefer tezetawoch.
ቀበና ሰፈሬ
ቀበና ሰፈሬ እትብቴ ያለብሽ
አስቆጠርኲ ዓመታት ከራቅሁ ካጠገብሽ
እንደምን ከርመሻል? እስቲ ልጠይቅሽ
ከራቅሁሽ ጀምሮ ምን ለውጥ እንዳሳየሽ
እንዴት ነው ሁኔታሽ ዝቅ አልሽ ተሻሻልሽ
ቀነሰ ጨመረ ቁጥሩ የነዋሪሽ።
ስምሽን መጠሪያ አርገው የሚፈሱት
እነዚያ ወንዞችሽ በጋ ኮለል ያሉት
ክረምት በጎርፋቸው የሚያጥለቀልቁት
ያበረክታሉ ዛሬም አገልግሎት?
እኔማ ሳድግብሽ ያሳየሽኝ ፍቅር
ከቶ የማይጠፋ እስከ ዕለት መቃብር
ሜዳሽ ላይ ዘልዬ የቧረኩበት
ከአብሮ አደጎቼ ጋር የዘለልኩበት
የብይ ጨዋታው ሞር ይሁን ወይ ቀስት
በመቆጠር እዳ የምገባበት።
የቡሄ ጭፈራው ዞሮ በየቤቱ
ሳንቲም በገንዘብ ያዥ፤ ዳቦውን ባንሶላ፤ በጀርባ ማንገቱ
ዳቦውንም ሸጦ፤ ሳንቲሙን ተካፍሎ፤ ቁማር መጫወቱ
ኦፕሬሽን ዳቦ፤ ወይ ፓስቴ ብስኩቱን፤ በልቶ መደሰቱ
ይህ ባንቺ ላይ ሳድግ ያለፍኩት ሁኔታ
ደም ስሬ ውስጥ ጠልቆ፤ አስሮኝ በትዝታ
ሊጠፋ የማይችል ሆነብኝ በሽታ።
መስከረም ሲጠባም አደዩ መፍካቱ
የእህቶች ጭፈራን፤ ከብረው ይቆዩኝን፤ ሰምቶ መደሰቱ
ቀለም ገዝቶ መጥቶ አበባ መስራቱ
አድባርም ሲደርስ ንፍሮውን ቂጣውን ተሻምቶ መብላቱ።
ታቦት አስገብቶ ጥምቀት በመድረሱ
እሳት እየሞቁ ማደር በየዳሱ።
የኳስ ጨዋታውስ፣ ወገን ተከፋፍሎ
ማዶን፣ ሀኪም ሜዳን፣ ጃልሜዳን አካሎ
ቃኘው በኮሪያስ ሲሸነፍ ስናዝን ሲያሸንፍ ስንጨፍር
ማታ ነው ድሌ እያልን ስንገባ ከሰፈር።
ዘፈን ትያትሩስ የምናሳያቸው
እነ አቫንቴ ሆኑ እነሾላ ፍሬው
በአባቱ ዳፋ በሰው ድግስ ያለው።
ይህ ባንቺ ላይ ሳድግ ያለፍኩት ሁኔታ
ደም ስሬ ውስጥ ገብቶ አስሮኝ በትዝታ
ሊጠፋ የማይችል ሆነብኝ በሽታ።
ኧረ ስንቱን ላስታውስ ካለብኝ ትዝታ
ቀበና ላይ ሳድግ ካካበትኩት ደስታ
ጊዜው ሳይቀየር ሀዘን ሳይበረታ
ወላጅ ልጁን አጥቶ ምሬቱ ሳይበዛ
ጔደኞች ሳያልቁ ሳይረግፉ እንደዋዛ።
ጌትነት የማነ፣ በለጠ አየለ፣ ያ ሞገስ ማሞና ፀጋዬ ቶሎሳን ገና ሳናጣቸው
አክሊለ አባተን፣ ዘውዱ በቀለና ሙሉጌታ ሞላን ሳናለቅስላቸው
ብርሃነ ከበደ፣ ከበደ አጐናፍር፣ አስማረ ሀጎስን ቀብር ሳንቀብራቸው
አማኑኤል ሣህለማሪያም፣ ወንድምአገኝ መኮንን፣ ያ ፈቃዱ ማሞን
ብናኝ አፈር እንኴን ሳንበትንላቸው፤
ጊዜው ሳይፈቅድልን ወግ ባናሳያቸው
ቢለዩም ከመሃል ባይኖር አካላቸው
ምን ጊዜም ቀበና ነውና እትብታቸው
ዘለዓለም ይቆያል ከኛ ትዝታቸው
ሁሌም የቀበና ቤተሰቦች ናቸው።
ሰለሞን (ጋንፉር